Amharic

http://media.sbs.com.au/podcasts/itunes/Amharic.png

Australian and international news and information in Amharic.

0 Likes     0 Followers     1 Subscribers

Sign up / Log in to like, follow, recommend and subscribe!

Website
http://www.sbs.com.au/podcasts/yourlanguage/amharic/
Description
Australian and international news and information in Amharic.
Language
🇬🇧 English
last modified
2019-03-18 19:52
last episode published
2019-03-18 08:20
publication frequency
3.14 days
Contributors
SBS Radio author  
Explicit
false
Number of Episodes
684
Rss-Feeds
Detail page
Categories
Society & Culture Sports & Recreation History TV & Film News & Politics Music Amateur

Recommendations


Episodes

Date Thumb Title & Description Contributors
18.03.2019

“የእኔ ሽበት” ማትያስ ከተማ (ወለላዬ)

ገጣሚ ማትያስ ከተማ (ወለላዬ)፤ በቅርቡ ለህትመት ስላበቃው “የእኔ ሽበት እና ሌሎች ግጥሞች” አዲስ የሥነ ግጥም መድብሉ ይናገራል።
18.03.2019

ቃለ ምልልስ - አርቲስት እና ሰአሊ ታምራት ገብረ ማርያም

የአፍሪካውያን ነፍስ እና መድብለ ባህል በሚል ስያሜ ያዘጋጃቸውን  የስእል ትእይንቶች ( ኤግዚቤሽኖች) በሜልበርን በማሳየት ላይ ይገኛል።በስራዎቼ የአፍሪካውያንን  ታሪክ መንገርና ፤ ለአውስትራሊያ  ማህበረሰብ  እያበረከቱት ያለውን አስተዋጻኦ ማሳየት እፈልጋለሁ ይላለ አርቲስት እና ሰአሊ ታምራት ገብረ ማርያም።
16.03.2019

African Australia Inclusion Program: Embet Tadesse and Yohannes Tafesse

ወ/ሮ እመቤት ታደሰና አቶ ዮሐንስ ታፈሰ፤ ማርች ፳ ለ፲ኛ ጊዜ ስለሚከበረው የአፍሪካውያን -  አውስትራሊያ አካታች ፕሮግራም ዓላማና የግል ሙያዊ ተሞክሮአቸውን አስመልክተው ይናገራሉ።
15.03.2019

“ዋ ሃገሬ” - ድምፃዊት ሰብለ ፈለቀ

ድምፃዊት ሰብለ ፈለቀ፤ አዲስ ስላወጣችው “ዋ ሃገሬ” ነጠላ ዘፈኗ ታወጋለች።
15.03.2019

“ዋና ዓላማችን የተሻለች አገር ማየት ነውና፤ እስከዛሬ የባከነውን የዳያስፖራ አቅም ወደ ጥቅም ለመለወጥ የሁሉንም ትብብር እንሻለን።” - ሰላማዊት ዳዊት

ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፤ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ (ኢዳኤ) ዋና ዳይሬክተር፤ ስለ ኤጀንሲው ዓላማ፣ ተግባራትና ትልሞች ያስረዳሉ።
13.03.2019

Settlement Guide: Should you build or buy your house?

ምንም እንኳ በቅርብ ዓመታት ውስጥ የቤት ባለቤትነት ቢቀንስም፤ የአውስትራሊያውያን አንዱ ሁነኛ የሕይወት አካል ሆኖ አለ።ተሰርቶ እየተኖረበት ያለ ቤት ይግዙ ወይም አዲስ ቤት ያሰሩ በኤክስፐርቶች አተያይ ሁለቱም ጠቀሜታዎች አሏቸው። 
11.03.2019

Early voting features early as NSW poll nears

ለማርች 23ቱ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ምርጫ የቅድሚያ ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ከወዲሁ ተከፍተዋል።የምርጫ ኤክስፐርቶችም 1.5 ሚሊየን ያህል መራጮች ከምርጫው ቀን ቀድመው ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ግምታቸውን አሳድረዋል። 
11.03.2019

New Boeing plane design under scrutiny after fatal crash

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 302 ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ናይሮቢ አቅንቶ አየር ላይ በተንሳፈፈ በስድስተኛው ደቂቃ የመከስከስ አደጋ ገጥሞታል።በሳቢያውም የአንድም ተሳፋሪ ሰው ሕይወት አልተረፈም።
11.03.2019

“ኢሕአዴግ ግንባር ሆኖ መቀጠል የለበትም፤ ወደ አገራዊ ፓርቲነት መቀየር አለበት ብለው የወሰኑት አራቱም ድርጅቶች ናቸው።” - ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም

አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፤ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ዋና አስተባባሪ ሚኒስትር፤ ኢሕአዴግን ወደ አገራዊ ሕብረ-ብሔራዊ የፖለቲካ ፓርቲነት ለመለወጥ ግድ ያሰኙ አንኳር ወቅተኛ አስባቦችና ፋይዳዎችን አንስተው ይናገራሉ።
10.03.2019

“ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የቀድሞው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዕርቀ ሰላም ኮሚሽኑ ቢገለሉ መልካም ነው።” - አክሊሉ ወንድአፈረው

አቶ አክሊሉ ወንድአፈረው፤ “የብሔራዊ ዕርቅ ኮሚሽን አበረታችና አሳሳቢ ገጽታዎች፤ የእርቀ ሰላሙ ጅምር ውጤታማነትን ከፍ ለማድረግ ምን ይደረግ?” በሚል ርዕስ ስላቀረቡት መጣጥፍ ያስረዳሉ።አቶ አክሊሉ ወንድአፈረው፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እሥረኞች አንድነት ኮሚቴ በካናዳ ሊቀ መንበር ናቸው።
8.03.2019

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን - 2019

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በየዓመቱ ማርች ፰ በመላው ዓለም የሴቶች ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ማኅበራዊ አስተዋጽዖዎቻቸውን፣ የትግል እንቅስቃሴዎችና ስኬቶቻቸውን በመዘከር ተከብሮ ይውላል።
7.03.2019

Migrant women find independence and more rights in Australia

አዲስ ይፋ በሆነ አንድ የሕዝብ አስተያየት ስብስብ መሰረት አያሌ መጤ ሴቶች ከትውልድ አገራቸው ይልቅ አውስትራሊያ ውስጥ ግላዊ ነፃነት፣ ማለፊያ ጤና፣ ሃብትና መልካም ዕድሎች ገጥሟቸዋል።አያሌ ሴቶች ከትውልድ አገራቸው ይልቅ አውስትራሊያ ውስጥ የበለጠ መብቶችን እንደተጎናጸፉ፤ በገንዘብ በኩልም ራሳቸውን የቻሉና የተሻለ ሕይወትም እየመሩ እንደሆነ ተናግረዋል።
7.03.2019

“በለወጡ ሳቢያ የመንደርና የጎሳ ፓለቲካ አክትሞ፤ ኢትዮጵያ እንደ ኢትዮጵያ ትኖራለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን።” - አቶ ባዩህ በዛብህ

አቶ ባዩህ በዛብህ፤ የጎንደር የሰላምና የልማት ምክር ቤት ሰብሳቢ፤ በጎንደርና አካባቢው ስፍኖ ስላለው ሰላምና እየረገበ ስላለው ውጥረት ይናገራሉ።
4.03.2019

ኪም ላቭግሮቭ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያ የክብር ቆንሱላ ሆነው ተሰየሙ

በኢትዮጵያና አውስትራሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርና ተጨማሪ ግልጋሎቶችንም ለመስጠት ይቻል ዘንድ የኢፌዴሪ መንግሥት በሜልበርን - ቪክቶሪያ የቆንሱላ ጽህፈት ቤት ከፍቷል። አቶ ኪም ላቭግሮቭም የክብር ቆንሱላ ሆነው ተሰይመዋል።
4.03.2019

ሌበርና የፌዴራል መንግሥቱ ለቤት ውስጥ አመፅ ተፈናቃዮች እገዛ ሊያደርጉ ነው

በመጪው የፌዴራል ምርጫ የሌበር ፓርቲ አሸንፎ መንግሥት ካቆመ፤ የአውስትራሊያ አውራ ባንኮች ከቤተሰብ አመፅ ለሚሸሹ አውስትራሊያውያን ማገዣ ፕሮግራም ድጎማ እንዲያደርጉ ግድ ይሰኛሉ።ሌበር ፓርቲ አመፅ ከታከለበት ግንኙነት ሸሽተው ለሚወጡ ሰዎች መደገፊያ የሚሆን 20 ሺህ ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቷል።
4.03.2019

Female CEOs 80 years from equal representation

የሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ከወንዶች አቻቸው ጋር እኩል የአመራር ተሳትፎ ላይ ለመድረስ 80 ዓመታት እንደሚፈጅባቸው አዲስ ይፋ የሆነ ዳታ ያመለክታል።በአሁኑ ወቅት በዋና ሥራ አስፈጻሚ ኃላፊነት ላይ የሚገኙ ሴቶች ክፍያ ከወንዶች በ162,000 ዶላርስ ያነሰ ነው።ዝቅተኛ በሆነ የሥራ አስኪያጅ ሥራ ላይ ያሉ ሴቶች መሳ-ለመሳ እኩል ሚና ማግኘቱ ላይ እንደሚደርሱ ቢጠበቅም፤ እነሱም ከወንዶቹ በ32,00...
3.03.2019

“ሸንጎው ከሌሎች መሰል የፖለቲካ ድርጅቶችጋር ተዋህደን አማራጭ የፖለቲካ ኃይል ሆነን እንድንወጣ እዚህ አድርሶናል።” - ወ/ሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታ

ወ/ሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታ፤ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ መድኅን ፓርቲና የኢትዮጵያ የጋራ ትግል ሸንጎ ምክትል ሊቀመንበር፤ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለመዋሃድ እያካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ፣ የለውጡን ሂደት አቅጣጫና ማርች ፰ የሚከበረውን ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክተው ይናገራሉ።
1.03.2019

“እንደ እኔ ጥናት፤ በአድዋ ጦርነት ከኢትዮጵያ ጦር ይልቅ የአድዋን ገጸ ምድር ለወታደራዊ ስልት የተጠቀሙት ጣልያኖች ናቸው።” - ዶ/ር ዳንኤል ካሣሁን

ዶ/ር ዳንኤል ካሣሁን፤ በቴክሳስ ኦስተን ኮሌጅ የቶፖግራፊ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ በአድዋ ጦርነት ለወታደራዊ ድሉ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ስለነበረው አስተዋጽዖ ይናገራሉ።ዶ/ር ካሣሁን፤ በ “Journal of Afroasiatic Languages, History and Culture” ላይ “Analyzing the Battle of Adwa through a spital prism” የሚል መጣጥፍ አቅርበዋል::
27.02.2019

Viva: Superfoods and you

ምናልባትም ለጤና ትድግና ከሚበጁ ልዕለ ምግቦች ውስጥ ስለ ቅጠል ጎመንና የእርድ ላቴ ሰምተው ይሆናል።የምግብ ተጠባቢዎች የተመጣጠነ ምግብ ለጤናማ የዕድሜ መግፋት እንደሚያግዝ ይመክራሉ።በእርግጥ፤ ልዕለ ምግቦችን መመገብ ከሌሎች ምግቦች የተሻለ ይጠቅም ይሆን? 
25.02.2019

“ከወታደራዊ ድሉ ባሻገር የአድዋ ድል ዋነኛ ፋይዳዎች፤ አገራዊ ዕሳቤ፣ ነፃነት፣ አንድነትና ሕብረ-ብሔራዊነት ናቸው።” - ዶ/ር ሺመልስ ቦንሳ

ዶ/ር ሺመልስ ቦንሳ ጉለማ፤ በStony Brook ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ የአፍሪካ ታሪክና ፖለቲካ ረዳት ፕሮፌሰር፤ ስለ አድዋ ድል አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ፋይዳዎች ይናገራሉ።
25.02.2019

“ዋ አድዋ!” - በብላቴን ጌታ ጸጋዬ ገብረመድኅን

ግጥም - ብላቴን ጌታ ጸጋዬ ገብረመድኅንድምፅ - አርቲስት ተስፋዬ ገብረሃና
25.02.2019

Major parties commit millions for heart health checks

የፌዴራል መንግሥቱና ሌበር ፓርቲ ለልብ ጤና ምርመራ የሚውል በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር በጅተዋል።ከኤፕሪል ፩ ጀምሮ ለልብ ሕመም የተጋለጡ አውስትራሊያውያን በሜዲኬይር የሚደጎም የልብ ጤና ምርመራ ማድረግ ይችላሉ።ይህም በጤና ባለ ሙያዎች ዕሳቤ በአሥር ሺህዎች የሚቆጠር የልብ ድካምን ለመከላከልና በሺህዎች የሚቆጠሩ ሕይወቶችን ለመታደግ ያበቃል።
24.02.2019

“ ወደፊት ለመራመድ ‘የኢትዮጵያ ስፖርት ከየት ወዴት?’ የሚል ሰነድ አዘጋጅተናል።” - ሚኒስትር ደኤታ ሃብታሙ ሲሳይ

የኢፌዴሪ የባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ሃብታሙ ሲሳይ፤ የኢትዮጵያን ዘመናዊ የስፖርት ታሪክ፣ ስፖርቱ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች፣ የገጠሙትን ተግዳሮችና የሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ የኢትዮጵያን ስፖርት ለማሳደግ የወጠናቸውን ትልሞች አስመልክተው ይናገራሉ።
22.02.2019

Samsung in battle to boost smart phone sales

የጮሌ ስልክ ኢንዱስትሪው፤ ሸማቾች አዲስ ስልክ እንዲገዙ ለማማለል ትግል ላይ ነው።ሶስቱ ዋነኛ የስልክ አምራቾች ሳምሰንግ፣ ኹዋዌይና አፕል የገበያ ድርሻቸውን ከፍ ለማድረግ ጉሮሮ ለጉሮሮ ያያ-ያዘ ፍልሚያ ላይ ናቸው።
22.02.2019

Julie Bishop to retire from parliament at upcoming federal election

የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ገዲብ የሊብራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ጁሊ ቢሾፕ፤ ከፖለቲካው ዓለም እንደሚጠወሩ አስታወቁ።በሳቢያውም፤ በመጪው የፌዴራል ምርጫ የምዕራብ አውስትራሊያውን የከርተን ምክር ቤት ወንበር ወክለው አይወዳደሩም።
21.02.2019

የኢትዮጵያ ሴቶች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምስረታ፤ ወ/ሮ የሐረርወርቅ ጋሻውና አቶ ዜና በለጠ

ወ/ሮ የሐረርወርቅ ጋሻው፤ የኢትዮጵያ ሴቶች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚደንትና አቶ ዜና በለጠ፤ የኢትዮጵያ ሴቶች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ፕሬዚደንት፤ ስለ ፓርቲው ምስረታ፣ ዓላማና ግቦቹ ይናገራሉ።
18.02.2019

“ምርጫን ማራዘም የሕግ መሰረትም፤ የክርክር ፍሬ ሃሳብም የለውም።” - ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ - ክፍል ፪

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር፤ ስለ ንቅናቄው ዓላማና ግቦች፣ የማንነት ፖለቲካ የአገር አቀፍ ምርጫና የወቅታዊውን የኢትዮጵያ ጉዳዮች አንስተው ይናገራሉ።
18.02.2019

Women from diverse cultural backgrounds face cyber attacks alone

ባሕላዊ ዝንቅነት ያላቸው ማኅበረሰብ አባል ሴቶች ቴክኖሎጂያዊ ግፊ፣ ወሲባዊ ክትትል፣ የዳታ ስርቆትና የኦንላይን ዛቻዎች በርክተው እየገጠሟቸው ነው።አንድ በቅርቡ የተካሄደ ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ የቪዛ ጉዳዮች፣ ሐፍረትና የቋንቋ ክህሎት ማነስ ችግሮቻቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖዎች አሏቸው።
18.02.2019

“ከኢትዮጵያዊነት አንሸሽም” - ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ - ክፍል ፩

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር፤ ስለ ንቅናቄው ዓላማና ግቦች፣ የማንነት ፖለቲካና የወቅታዊውን የኢትዮጵያ ጉዳዮች አንስተው ይናገራሉ።
17.02.2019

Viva: How to succeed at online dating?

የኦንላይን የፍቅር ግንኙነት መቀጣጠሪያ ባለ በርካታ ቢሊየን ዶላር ኢንዱስትሪ ነው። ይሁንና ተፈላላጊዎችን አገናኝ ባለሙያዎች፤ የሳይበር ዓለሙ ፍቅር ፍለጋ ለስኬት የሚበቃው ልቦችና አዕምሮዎቻቸውን እንደምን መከተል እናዳለባቸው ለሚያውቁቱ መሆኑን ይናገራሉ።እርስዎስ፤ በኦንላይን ዓለም አዲስ የፍቅር ግንኙነት ለመመስረት ሲነሳሱ በታሳቢነት ልብ እንዲሉ የሚያሻዎት ምንድነው?
15.02.2019

PM promises Hakeem Al-Araibi citizenship is 'not too far away'

የአውስትራሊያን ምድር ከረገጠ ጥቂት ቀናት በኋላ ሐኪም አል-አራቢ በአገሪቱ መሪዎች ካንብራ ፓርላማ ውስጥ ‘እንኳን ደህና መጣህ’ ተብሏል።አል-አራቢ ሸሽቶ ባመለጣት አገር- ባህሪን ‘ተይዞ ይምጣልኝ’ አቤቱታ ሳቢያ ለሁለት ወራት ዘብጥያ ወርዷል።የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾችና ፖለቲከኞች የሐኪም ይለቀቅ ዘመቻ እያደረጉ ሳለ፤ ባህሪን ባለፈው ሰኞ የሐኪምን ተይዞ ወደ አገር መመለስ አልሻም ስትል ድንገት ...
15.02.2019

“ወላጆች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ጥቅምን አስመልክቶ እንዲያስተውሉ ጥሪ ማድረግ እፈልጋለሁ።” - ዶ/ር ተፈሪ የሺጥላ

ዶ/ር ተፈሪ የሺጥላ፤ የቪክቶሪያ ቋንቋዎች ትምህርት ቤት - በካሮላይን ስፕሪንግ የክሪክሳይድ ኮሌጅ ቅርንጫፍ የአማርኛ ቋንቋ አስተባባሪ፤ ስለምን የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት መመስረት እንዳስፈለገና እነማን ተጠቃሚዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይናገራሉ።
15.02.2019

“ለውጡ ትግራይ ውስጥ እንዲገባ እንቅስቃሴ እያደረግን ነው ያለነው።” - ዶ/ር አረጋዊ በርሄ

ዶ/ር አረጋዊ በርሄ - የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) ሊቀመንበር፣ ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን - የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) ምክትል ሊቀመንበርና አቶ መኮንን ዘለለው - የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፤ ድርጅታቸው ትዴት ስለምን ወደ አገር ቤት ገብቶ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የለውጥ ሂደት ለመሳተፍ እንደወሰነ፣ ድርጅቱ እያካሄደ ስላው ፖለቲ...
14.02.2019

Settlement Guide: How to get involved in your children's school?

ወላጆች በልጆቻቸው ትምህርትና ትምህርት ቤት ተሳትፎ ሲያደርጉ፤ ለልጆቻቸው ውጤት፣ ከትምህርት ቤት አለመቅረትና ጠቅላላ ጤና ላይ ማለፊያ አስተዋጽዖዎች ይኖራቸዋል።ይሁንና ለአውስትራሊያ እንግዳ የሆኑ ወላጆች ምናልባትም ከየት መጀመር እንዳለባቸው ልብ ይላሉ።
11.02.2019

“በአቶ ገዱና ዶ/ር ደብረጽዮን መካከል ያለው ግንኙነት ጓዳዊ ነው።” - አሰማኸኝ አስረስ - ክፍል ፪

አቶ አሰማኸኝ አስረስ፤ የአማራ ክልላዊ መንግሥት - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤ በአማራና በትግራይ ክልል መንግሥታት፣ በአማራ ክልል መንግሥትና በኤርትራ መንግሥት መካከል ስላሉት ግንኙነቶች፤ ባሕር ማዶ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ክልላቸው የሚጠብቃቸውን ሁለገብ ተሳትፎዎች አስመልክተው ይናገራሉ።  
10.02.2019

“ኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደውና በአማራ ክልል ውስጥም የተመነዘረው ለውጥ ያስገኛቸው ሁለት ዋነኛ ነገሮች ነፃነትና ተስፋ ናቸው።” - አሰማኸኝ አስረስ - ክ

አቶ አሰማኸኝ አስረስ፤ የአማራ ክልላዊ መንግሥት - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ስላለው የለውጥ እንቅስቃሴ፣ የማንነትና የወሰን ጥያቄዎች፣ እንዲሁም፤ የእነ አቶ በረከት ሰምዖንንና አቶ ታደሰ ካሳን ለእሥር የመዳረግ አስባቦች አንስተው ይናገራሉ።  
8.02.2019

“ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን የጦር ወንጀል በመቃወም የካቲት ፲፪ን በያለንበት ልናከብር ይገባናል።” - አቶ ኪዳኔ ዓለማየሁ

አቶ ኪዳኔ ዓለማየሁ፤ የዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ - የኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ የካቲት ፲፪ የሰማዕታት ዝክረ መታሰቢያ ፋይዳና ድርጅታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ስላቀረበው አቤቱታ ይናገራሉ።
6.02.2019

The History of Chinatown

በዓለም ዙሪያ በርካታ ዋና ከተሞች የቻይና ከተማ አሏቸው። በአብዛኛው የተቆረቆሩትም ከቻይና ውጪ የመጀመሪያ ቻይናውያን ሰፋሪዎች በከተሙባቸው ቀዬዎች ነው።ነፀብራቅነታቸውም ተስፋና እንግልትን፤ በርካታ መጤዎች አገራቸውን ለቅቀው፤ ባሕር አቋርጠው ሲሄዱ የሚገጥማቸውን የአዲስ ሕይወት የኑሮ ትግል ነው።
4.02.2019

ቃለ ምልልስ -ክቡር ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ

 ክቡር ዶ/ር አርቲስ ሙላቱ አስታጥቄራስን ፈልጎ የማግኝት ጥያቄንው በመለሰለት በኢትዮ ጃዝ የሙዚቃ ስልት ፈጣሪነት እና አባትነት ነው ባለም ዙሪያ የሚታወቀው ። እነሆ ስልቱ  ክግማሽ ምእት አመት በላይ አስቆጥሮ ኢትዮጵያን በአለም ዙሪያ እያስጠራት ይገኛል።" ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ነች ባህልን በተመለከት ለአለም ብዙ ነገር ያበረከተች ነች ።ይህንን ስል ክውዝዋዜ ከሙዚቃ መሳሪዎⶭን እና ከፈጣሪዎቻቸ...
4.02.2019

“ኢሳት ለሀገሬ” - ሐና ለገሰ

ወይዘሮ ሐና ለገሰ፤ የ “ኢሳት ለሀገሬ” ዝግጅት ሊቀመንበር፤ የካቲት ፱ በሚሊንየም አዳራሽ ስለሚካሄደው ልዩ ዝግጅትና ተጋባዥ እንግዶች ይናገራሉ።
4.02.2019

The Evolution of Lunar New Year

ፌብሪዋሪ ፭ በአያሌ አውስትራሊያውያን ዘንድ ከአዘቦታዊ ቀንነት ያለፈ ረብ አይኖረው ይሆናል። ለቻይናውያን፣ ቬትናማውያንና ኮሪያውያን ግና የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ዕለት ነው።
3.02.2019

VIVA: Should I pay for my grandchildren’s school fees?

የትምህርት ወጪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ በመምጣቱ በርካታ አያቶች ለትድግና የችሮታ እጆቻቸውን እየዘረጉ ነው።በ2018 የተወለዱ ህፃናትን ከሙዋዕለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ወደ ግል ትምህርት ቤት ልኮ ለማስተማር ግማሽ ሚሊየን ዶላርስ ያህል ወጪን ግድ ይላል።በትላልቅ ከተሞች ከሆነ ደግሞ ወጪው ከዚያም ይልቃል።የሕይወት ዘመን እየረዘመ፤ ወጪ እየናረ ባለበት ወቅት የመጠወሪያ ጥሪትን ላለሟሟጠጥ መላ ...
1.02.2019

ቃለ ምልልስ -ክቡር ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ

ክቡር ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በአውስትራሊያ ታላላቅ ከተሞች የሙዚቃ ስራውን በማቅረብ ላይ ይገኛል። በቆይታውም ሜልበርን በሚገኘውን የኤስ ቢ ኤስ ራድዮ ጣቢያ በመገኝት ከአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጋር በሙዚቃ ስራዎቹ ዙሪያ ቆይታን አድርጓል።ክቡር ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በተለይ የሚታወቀው በኢትዮ ጃዝ የሙዚቃ ስልት ፈጣሪነት እና አባትነት ነው። እንደ እሱ አባባል ከሆነ " እኔ ራሴን ...
28.01.2019

ቃለ ምልልስ- አርቲስት ሶስና ወጋየሁ በዘንድሮው የአውስትራሊያ ቀን "ኦርደር ኦፍ አውስትራሊያ" የክብር ሽልማት ተሸላሚ

አርቲስት ሶስና ወጋየሁ የጋሞ ሰርከስ ስኩል ኦፍ ኢትዮጵያ ዋና ሃላፊ በዘንድሮው የአውስትራሊያ ቀን ፤የኦርደር ኦፍ አውስትራሊያ የክብር ሽልማት ተሸላሚ ሆናለች።ይህ ሽልማት በአውስትራሊያ የአገረ ገዥ መስሪያ ቤት በየአመቱ ለማህበረሰቡ ታላቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ዜጎች ይበረከታል።አርቲስት ሶስና በተለይም በሰርከስ ሙያዋ አውስትራሊያን በአለም አቀፍ መድረኮች በመወከል፤ የነባር ህዝቦችን በመርዳት ፤ ...
28.01.2019

ቃለ ምልልስ - አቶ ሀይለ ልኡል ገብረ ሰላሴ በዘንድሮው የአውስትራሊያ ቀን "ኦርደር ኦፍ አውስትራሊያ" የክብር ሽልማት ተሸላሚ

አቶ ሀይለ ልኡል ገብረ ስላሴ የአፍሪክውያን ቲንክ ታንክ መስራች አባል እና የወቅቱ ሊቀመንበር አንዲሁም በቪክቶርያ ፖሊስ የአፍሪካውያን ግብረ ሃይል ሰብሳቢ ፤ በዘንድሮው የአውስትራሊያ ቀን ፤የኦርደር ኦፍ አውስትራሊያ የክብር ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።የዚህን ሽልማት ሂደት የአውስትራሊያ የአገረ ገዥ መስሪያ ቤት የሚመራው ሲሆን ፡በየጊዜውም ከተለያዩ ቦታዎች የሚደርሱትን ጥቆማዎች በማጣራት እና የእማ...
25.01.2019

ወቅታዊ ጉዳዮች - የአውስትራሊያ ቀን

አውስትራሊያ በይፋ ከጋራ ብልጽግና አገሮች ተርታ ውስጥ የገባችው ከጃንዋሪ 01/ 1901 አም በኋላ ቢሆንም ለሌሎች ዜጎች የአውስትራሊያዊነት ዜግነትን መስጠት የጀመረቸው ግን ከጃንዋሪ 26/1949 በኋላ ነበር።የመጀመሪያዎቹም ዜግነት ተቀባዮች ሰባት ወንዶች ነበሩ።.
25.01.2019

ቃለ ምልልስ -መጋቢ ሃይማኖት ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ

ከመጋቢ ሃይማኖት ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ በዋሽንግተን ዲሲ የርእሰ አድባራት ደበረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ሀላፊ ጋር ፤ ስለ አውስትራሊያ  ቆይታቸው ፤ በሜልበርን ለጥምቀት በአል የአራቱን  አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ለማመጣት ሰለተጫወቱት ሚና፤  የሲኖዶሱን አንድ መሆን ተከትሎ የታየውን የአብያተ ክርስቲያነት  እና የምእመናንን ህብረት ለማስቀጠል የሐይማኖት አባቶች ድ...
21.01.2019

በአውስትራሊያ -ሜልበርን የጥምቀት በአል አከባበር ቅኝት

የጥምቀት በአል በአውስትራሊያ ከጃኑዋሪ 19 -20 ,2019  በሜልበርን ከተማ በፉትስክሬ ፓርክ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። በዚህም የሜልበርን ደብረሰላም መድኃኔዓለም  ፤ የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ፤የመካነ ሰላም ቅደስት ልደታ ለማርያም በኢ/ኦ/ተ/ ቤ/ክ ሜልበርን አውስትራሊያ እና የመራተ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት አብያተ ቤተክርስቲያናት በጋራ አክብረዋል። በስፍራውም ብጹእ አቡነ ጴጥ...
18.01.2019

ምልሰታዊ ምልከታ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶሶች አንድነት

ባለፈው በፈረንጆቹ 2018 አ.ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በኢትዮጵያ ከተከናወኑት አበይት ተግባራት መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶሶች አንድነት ነበር።በወቅቱም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአውስትራሊያና በኒውዝላንድ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ በርናባስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ...
14.01.2019

በሜልበርን አራቱ አብያተ ክርስቲያናት የመጪውን የጥምቀት በአል በጋራ ለማክበር ተስማሙ።

በሜልበርን አራቱ አብያተ ክርስቲያናት የመጪውን የጥምቀት በአል በጋራ ለማክበር ተስማሙ። ስምምነቱም የተደረሰው የቤተክርስቲያን አንድነት ከታወጀ እና ቅዱስ ሲኖዶሱ አንድ ከሆነ በኋላ መከፋፈሉ ሀይማኖታዊም ሆነ ቀኖናዊ ያለመሆኑን የአብያተ ክርስቲያናቱ ተውካዮች እና ምእመናኑ ሰላላመኑበ መሆኑን የምስራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ ተናግረዋ። የጋራ ወይይቱን...